እዚህ ያለሁኝ ለምንድነው?

 

ይህ ግምገማ የልጅዎ አስተማሪ ልጅዎ ምን ያህል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ እንዳለው እንዲያውቅ ይረዳል።

 

ኤልኤል ምንድን ነው?

 

ELL English language learning ማለት ነው። ትርጉሙም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ማለት ነው።

 

ልጄ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቃት እስኪኖረው ድረስ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

 

በአማካይ እስከ 7 ዓመታት ሊወስድ ይችላል።

 

ማህበራዊ ቋንቋ ብዙውን ጊዜ መጀመሪያ ያዳብራል፡ የአካዳሚክ ቋንቋ ለማደግ

ረዘም ያለ ግዜ ይወስዳል። በማህበራዊ እና በአካዳሚክ ቋንቋ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

 

ማህበራዊ ቋንቋ ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ስንነጋገር በየቀኑ የምንጠቀምበት ቋንቋ ነው።

 

የአካዳሚክ ቋንቋ በትምህርት ቤት ለማንበብ እና ለመጻፍ የምንጠቀምበት ቋንቋ ነው።

 

በቤት ውስጥ የእናት ቋንቋ መናገር መቀጠል አስፈላጊነቱ ምንድነው?

 

ጠንካራ የቤት ቋንቋ ችሎታ መኖር፡ ልጆች እንደ እንግሊዝኛ ሌላ ቋንቋ እንዲማሩ ይረዳቸዋል። ከሁሉም በላይ የቤትዎን ቋንቋ መጠበቅ ልጅዎ ከባህላቸው እና ከዘመዶቻቸው ቤተሰብ ጋር እንዲገናኝ ይረዳል።

 

የልጄን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት በቤት ውስጥ ለመደገፍ ምን ማድረግ እችላለሁ?

 

የቤትዎን ቋንቋ መናገርዎን በመቀጠል ልጅዎን መደገፍ ይችላሉ። ከልጅዎ ዕድሜና የእንግሊዝኛ ደረጃ የሚመጣጠን፣ የድርብ ቋንቋ መጽሐፍትን አብረው ማንበብ ይረዳል። ለጀማሪዎች የተዘጋጀ የድርብ ቋንቋ መጽሐፍትን በዚህ የኢንተርነት ድህረ-ገጽ ማግኘት ይቻላል www.storybookscanada.ca ። በበርነቢ የህዝብ ቤተ-መፃሕፍት የድርብ ቋንቋ መጽሐፍትንና በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉ መጻሕፍት ማግኘት ይቻላል።

 

የልጄ የቋንቋ ብቃት እንደገና የሚገመገመው መቼ ነው?

 

ልጅዎ በትምህርት ቤቱ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪቸው ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ይገመገማል። በእያንዳንዱ የትምህርት ዓመት መጨረሻ፣ አብዛኛውን ጊዜ ከሚያዝያ – ሰኔ ባለው ግዜ መካከል የሚደረግ መደበኛ ግምገማ አለ። ይህ ግምገማ በመደበኛ የትምህርት ቀን ውስጥ በልጅዎ ትምህርት ቤት ውስጥ ይከናወናል።

 

ልጄ በትምህርት ቤት ምን ዓይነት ድጋፎች ያገኛል?

 

ልጅዎ በትምህርት ቤት ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ኣስተማሪው እርዳታ ያገኛል። ይህ እርዳታ በክፍል ውስጥ ወይም በትንሽ ቡድኖች ውስጥ ሊሆን ይችላል። የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር እና የመማሪያ ክፍል መምህር ልጅዎን የሚደግፉበትን መንገድ በመወያየት አብረው ሊሠሩ ይችላሉ።